የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ በስምንት ወራት ከ221 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

By ዮሐንስ ደርበው

March 15, 2022

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 221 ቢሊየን 487 ሚሊየን 562 ሺህ 425 ነጥብ 97 ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ 240 ቢሊየን 338 ሚሊየን 604 ሺህ 387 ነጥብ 02 ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ ነው÷ 221 ቢሊየን 487 ሚሊየን 562 ሺህ 425 ነጥብ 97 ብር መሰብሰብ የቻለው፡፡

በዚህም የዕቅዱን 92 ነጥብ 16 በመቶ መፈፀም መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ገቢው ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር የ30 ቢሊየን 192 ሚሊየን 916 ሺህ 457 ነጥብ 64 ብር ወይም የ15 ነጥብ 78 በመቶ ዕድገት አለው ተብሏል፡፡

ገቢው የተሰበሰበውም ከሀገር ውስጥ ታክስ 131 ቢሊየን 121 ሚሊየን 378 ሺህ 475 ብር፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 90 ቢሊየን 366 ሚሊየን 183 ሺህ 950 ነጥብ 97 ብር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህ ገቢ የተሰበሰበው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አራት የተቋሙ ቅርንጫፎች ከሥራ ውጭ በሆኑበት እና በኮሮና ወረርሽኝና መሰል ተጨማሪ ችግሮች ውስጥ በመሆኑ ከእነዚህ እጅግ በጣም ጥሩ አፈፃፀም መሆኑም ነው የተገለጸው።