Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ከማንዋል አሰራር በማላቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና ቀልጣፋና ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ከማንዋል አሰራር በማላቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና ቀልጣፋና ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት አገልግሎት ገለጸ፡፡
 
የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት አገልግሎት የክልልና የከተማ መስተዳድሮች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራን ለመደገፍ ከዓለም ባንክ የተለገሱ ተሽከርካሪዎችን በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
 
በርክክቡ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው÷ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የሚያጠናቅረው ክቡር የሆነው የሰው ልጅን የተመለከተ መረጃ ነው፤
ይህም ከሌላ የመረጃ ምዝገባ ለየት ያደርገዋል ነው ያሉት።
 
አንድ መረጃ መረጃ የሚሰኘው ምስጢራዊነቱ ሲጠበቅ፣ ትስስር ሲኖረውና በወቅቱ ሲገኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ መሉጌታ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ከማንዋል አሰራር በማላቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
 
በሃገር አቀፍ ደረጃ በ1 ሺህ 380 ቀበሌዎች የሞባይል ኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስታቲስቲክስ የሙከራ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ መጀመሩም ተመላክቷል።
Exit mobile version