Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን ማለፊያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
 
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በዚህ መሰረት አንደኛ ዙር ተፈታኞችን በተመለከተ፡-
 
የተፈጥሮ ሳይንስ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለወንድ 363 እንዲሁም ለሴት 351
 
በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለወንድ እና ለሴት በተመሳሳይ 300
ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለመደበኛ ተፈታኞች ወንድ 351 እና ለሴት 339
 
ለግል ለወንድና ለሴት በተመሳሳይ 300
 
መስማት ለተሳናቸው ለሁለቱም ጾታ 300
 
በግል ለሚማሩ 300
 
ተፈጥሮ ሳይንስ የግል (ድጋሚ ተፈታኞች) ሁለቱም ጾታ 380
በግል ከፍተኛ ትምህርት መከታታል ለሚፈልጉ 300
 
ማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛ ተፈታኞች ወንድ 264 እና ለሴት 254 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል 250
 
አይነ ስውራን መደበኛ ተፈታኞች ለሁለቱም ጾታ 200 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል 200
 
ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 254 እና ለሴት 250 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሚፈልጉ 250
 
መስማት ለተሳናቸው ለሁለቱም ጾታ 250 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለሚከታተሉ ለሚፈልጉ 250
 
ማህበራዊ ሳይንስ የግል (ድጋሚ ተፈታኞች) ሁለቱም ጾታ 280 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለሚከታተሉ 250 መቁረጫ ነጥብ ሆኗል።
 
ሁለተኛ ዙር ተፈታኞችን በተመለከተ ፡-
 
የተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 423 እና ለሴት 409 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 350
 
በታዳጊ ክልሎች ለወንድ 410 እና ለሴት 396 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 350
 
አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 411 እና ለሴት 398 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታዎች 350
 
መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ጾታዎች እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል 350
 
የግል ተፈታኞች (ድጋሚ ተፈታኞች) ሁለቱም ጾታ 443 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል 355
 
ማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 317 እና ለሴት 305 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 300
 
ለአይነ ስውራን ሁለቱም ጾታዎች 250 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 250
 
ለታዳጊ ክልሎች ለወንድ 305 እና ለሴት 300 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁቱም ጾታ 300
 
ለአርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 306 እና ለሴት 300 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 300
 
መስማት ለተሳናቸው ለሁለቱም ጾታዎች 300 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሁለቱም ጾታ 300
 
ለግል ተፈታኞች (ድጋሚ ተፈታኞች) ለሁለቱም ጾታ 335 እንዲሁም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል 300 መቁረጫ ነጥብ ሆኗል።
 
በመሃመድ አሊ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version