የሀገር ውስጥ ዜና

ከ 71 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Feven Bishaw

March 14, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ 71 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 62 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡