Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ተሾመ ከቻይናው ምክትል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የባህልና ቱሪዝም ምክትል ሚኒስትር ዣንግ ዡ ጋር ተወያዩ።
 
በውይይታቸው ወቅትም በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየውን የቱሪዝም ዘርፍ መልሶ ማነቃቃት በሚቻልበትና በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን የባህልና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
 
በዚህ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑንና ግንኙነታቸውም በፈረንጆቹ 2017 ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂያዊ ትብብር ከፍ ማለቱ ተገልጿል።
 
ይህንንም በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በባህል ልውውጥና በቱሪስት ፍሰት በአፍሪካ ቻይና የትብብር ፎረም ማዕቀፍ ማነቃቃትና አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መጠቆሙን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
 
አምባሳደር ተሾመ ቻይና ለኢትዮጵያ ላደረገችው የኮቪድ19 ክትባትና የተለያዩ የህክምና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version