አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ እና የዩክሬን ተወካዮች ውይይታቸውን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሊቀጥሉ መሆኑን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል፡፡
እንደ ቃል አቀባዩ ገለፃ በውይይቱ የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አማካሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ የሩሲያ ልዑክን ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የዴቪድ አራካሚያ ደግሞ የዩክሬንን ልዑክ ይመራሉ ነው የተባለው።
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ቀደም ሲል ጉዳዩን አስመልከተው እንደተናገሩት የኪዬቭ ተወካዮች የተሳካ ውይይት እንዲደረግ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀናት በፊት ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሹልዝ ጋር በስልክ ባደረጉት ንግግር በቅርብ ቀናት ውስጥ በሩሲያ እና በዩክሬን ተወካዮች መካከል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይቶች እንደሚኖሩ ገልፀው ነበር፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን እስካሁን ሶስት ዙር የፊት ለፊት ውይይት በቤላሩስ ያካሄዱ ሲሆን ሁሉም ውይይቶች ያለስምምነት መጠናቀቃቸውን ሲ ጅ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!