Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት የመማር ማስተማር ስራው ተስተጓጉሎ የነበረው የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ዛሬ መቀበል ጀምሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ጥበቃና ደህንነት ሰራተኞች አስፈላጊውን የፍተሻ ስራ እያከናወኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ጀምረው ወደ ግቢ በመግባት ላይ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ እና የሚቀበል ሲሆን÷ ለተማሪዎቹም የትራንስፖርት አገልግሎት ማመቻቸቱን አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በመናኸሪያ፣ በፒያሳ፣ በአዳጎና ጎንደር በር ፌርማታዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version