Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚኒስትሮች ለብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ፣ አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በመልዕክታቸው ለተመራጮቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት ለተመራጮቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸው፥ የብልጽግና አባላትና አመራሮች ከጎናችሁ በመሆን ሀገራችን ያላትን ተስፋ የበለጠ የምናለመልምበት፣ የገጠሙ ተግዳሮቶችን በጋራ የምናስወግድበት፣ ለላቀ ትግልና ለላቀ ድል የምንነሳበት ምዕራፍ መሆኑ እምነቴ ነው ብለዋል::
መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ሚኒስትሮቹ ተመኝተዋል፡፡

Exit mobile version