Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዶክተር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የሶማሌ ህዝብ ካሳለፈው በደልና ግፍ በኋላ ዛሬ የብልጽግና ፓርቲ አቶ አደም ፋራህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል ብለዋል።
ይህ ትልቅ ድል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ወደፊት ለሚመጣው ስኬት እና ህዝቡ ለሚገባው ሰላም ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version