አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።
የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።
የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡
የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡
የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።
የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡
የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት መሆኑን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።