የሀገር ውስጥ ዜና

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ዶን ቤየር ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን እንደሚቃወሙ ገለጹ

By Meseret Awoke

March 09, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የኮንግረስ አባል የሆኑት ዶን ቤየር ‘ኤች አር 6600’ በሚል ኢትዮጵያን በሚመለከት የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ የተሳሳተ በመሆኑ እንደሚቃወሙት ተናግረዋል፡፡

የኮንግረስ አባል ቤየር ትናንት በማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ ፥ ረቂቁን ለመቃወም በቀጣይ ከአባላቱ ጋር በትብብር እና በቅንጅት እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጡት።

ረቂቅ ሕጉን ለማጽደቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ለሰላም መፈጠር ፣ ለምክክር እና ሰዎችን ወደ አንድ ለማምጣት የበለጠ አስቸጋሪ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

በአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ቶም ማሊኖውስኪ፣ ያንግ ኪም፣ ግሪጎሪ ሚክስ እና ማይክል ማካውል የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉም የኮንግረስ አባሉ ቃል ገብተዋል፡፡

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ለማስወጣት መወሰኗን አጥብቀው እንደሚቃወሙ አውስተው ፥ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት ለመመለስ ከዋና ዋና አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!