Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን ቡና እና የባህል እሴቶች ለቻይናውያን ለማስተዋወቅ የሚያስችል ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ቡና እና የባህል እሴቶች ለቻይናውያን ለማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በቻይና ከኢትዮጵያ ቡና ማዕከል ፕሬዚዳንት ዩዋንዌ ጉኦ ጋር ነው በጉዳዩ ላይ ውይይት ያካሄዱት፡፡
የቡና ማዕከሉ እ.ኤ.አ. ማርች 2019 በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲና በሆን ቼን የቴክኖሎጂ፣ ባህልና ኮሙኒኬሽን የጋራ ትብብር የተቋቋመ ሲሆን ÷የኢትዮጵያን ቡና ለቻይናውያን በማስተዋወቅና ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ተብሏል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version