Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የምታደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የሕግ አማካሪና የአፈጉባኤው ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ዘለቀ ተመስገን የፈረንሳይ ምክር ቤት የውጪ ጉዳዮች፣ የመከላከያና የደህንነት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ኦሊቨር ካዲክን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ለረዥም ጊዜ የቆየ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን ዶክተር ዘለቀ አስታውሰው÷የሀገራቱ ወዳጅነት አንድ ምዕተ ዓመት የተሻገረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሰረተ ልማትና በኢኮኖሚ ፈረንሳይ ያሳየችውን አጋርነት አድንቀዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱንና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይታቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ዶክተር ዘለቀ ያብራሩ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተፈጠረው አለመግባበትና ጦርነት በሰላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈታ የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኦሊቨር ካዲክን በበኩላቸው÷ የፈረንሳይ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version