አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ ሕዝቦች የባሕል ፌስቲቫል እና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ለማካሄድ ውይይት ተደረገ፡፡
በቀጣዩ መጋቢት ወር የሚካሄደው የባሕል ፌስቲቫል እና አውደ ርዕይ መርሃ ግብር ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኡጋንዳ፣ ርዋንዳ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የባሕል ኢንዱስትሪ ልማት ትብብር ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ተክሉ ፥ ባህልና ኪነጥበብ ለአገር ገጽታ ግንባታ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲቻል የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የማንነት መገለጫ የሆኑ ትዕይንታዊ ጥበባት አገልግሎቶችን፣ ዓይነተ-ብዙ ባሕላዊ የእደ ጥበብ ምርቶችን በማስተዋወቅ፣ በሀገር ውስጥና በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በባሕል እና በኪነጥበብ ፌስቲቫል በማሳተፍ፣ የልምድ ልውውጥ መድረክ በማዘጋጀት የባሕል ዲፕሎማሲንና ንግድና ቀጠናዊ ትስስር እንዲጎለብት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ከዘርፉ የሚገኘውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለማሳደግ ታስቦ የሚዘጋጅ መሆኑን ገልጸዋል።
ዕቅዱ ለሚኒስትሮችና ለሚመለከታቸው አካላት በገለጻ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዕቅዱም ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ድንቅ ባሕሎች፣ የተፈጥሮ ፀጋዎች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች ከምሥራቅ አፍሪካ ጋር በማስተሳሰር ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል ተብሎ የታመነበትና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች ትልቅ አጋጣሚን የሚፈጥር ‘’የምሥራቅ አፍሪካ’’ የባሕል ፌስቲቫል እና አውደርዕይ በአዲስ አበባ በወዳጅነት አደባባይ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ለማካሄድ ዝርዝር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!