አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሁድ ይፈፀማል ።
የሥርዓተ ቀብር አስፈጻሚ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ በጠቅላይ ቤተክህነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የአቡነ መርቆሬዎስን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም 12 አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ እና በስሩም 12 ንዑስ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል ።