Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን ማንኛውም ማዕቀብ ሩሲያን ጨምሮ ከማንኛውም ሃገር ጋር በሚኖራት ትብብር ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥርባት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንኛውም ማዕቀብ ቴህራን ሩሲያን ጨምሮ ከሌሎች ሃገራት ጋር በሚኖራት ትብብር ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዱላሂን ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት በዩክሬን ቀውስ እና ፀረ-ኢራን ማዕቀቦችን ለመቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ሚኒስትሩ የሚጣሉ ማዕቀቦችን ማስቀረት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በቪየና እየተደረገ ባለው ድርድር የሚደረሰው ስምምነትም ቴህራን የቅርብ አጋሮቿን ጨምሮ ከሌሎች ሃገራት ጋር ለሚኖራት ትብብር መሰረት ይጥላልም ብለዋል።
ጦርነትና ማዕቀቦችን እናወግዛለን ያሉት ሚኒስትሩ የሚጣል ማዕቀብ ሃገራቸው ሩሲያን ጨምሮ ከማንኛውም ሃገር ጋር በምታደርገው ትብብር ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ገልፀዋል።
የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው ኢራን እና ሩሲያ በተለይም በንግድ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በአገራቸው ላይ የተጣለውን ማዕቀብም አግባብነት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ፕሬስ ቲቪ በዘገባው አመላክቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version