የሀገር ውስጥ ዜና

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

By Feven Bishaw

March 07, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስቴርና የፌደራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን በደቡብ ምዕራብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ተገኝተው የቡና እደሳ ስራን ተመልክተዋል፡፡ የክልሉ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሀገሪቱ ቡና፣ ቅመማ ቅመምና ሻይ ለማምረት ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡