Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዳዲሶቹ አምባሳደሮች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ አገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን እንዲወክሉ ለተሾሙ አምባሳደሮች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቋል።
 
ዛሬ በተካሄደው የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል፡፡፡
 
አቶ ደመቀ አዳዲሶቹ አምባሳደሮች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ አገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
 
በሚመደቡባቸው አገራት ሁሉ የኢትዮጵያን ትክክለለኛ ገጽታ ለዓለም በማስታዋወቅ ወንድማማችነትን በመፍጠር ዓለም ኢትዮጵያን እንዲረዳ የማድረግ ትልቅ አገራዊ ሃላፊነት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
 
የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገርን የሚያኮራ ሥራ እንዲያከናውኑም አስገንዝበዋል።
 
ሥልጠናውን የተከታተሉ አምባሳደሮች በበኩላቸው፥ሥልጠናው የአገሪቷንና የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንደተሰጣቸውና በዚህም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በእውቀት ለመፈጸም እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
 
የአምባሳደርነት ሥራቸውንም በአግባቡ ለመፈጸም ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version