አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የውሃ ደህንነትና ዘላቂ ልማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው በአምስት ሀገራት የሚተገበረውን የውሃ ደህንነትና ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት መሰረት ያደረገ ሲሆን፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብሪታኒያ፣ ኮሎምቢያ፣ ህንድና ማሌዢያ የጉባኤው ተሳታፊዎች ናቸው።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ላይ የውሃ ደህንነትና ዘላቂ ልማትን ከማስፈን አንጻር ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።
በጉባኤው የሀገራቱን የውሃ ደህንነትና ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ውይይቶች የሚደረጉ ሲሆን፥ ሀገራቱ በውሃ ሃብት ደህንነትና ዘላቂ ልማት ላይ ያላቸውን ልምድ ይለዋወጣሉ።
ጉባኤው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃና መሬት ሃብት አስተባባሪነት ነው እየተካሄደ ያለው።
የመጀመሪያው ጉባኤ በማሌዢያ ተካሄዷል።
በየሽዋ ማስረሻ እና በታሪክ አዱኛ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision