Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚደግፍ ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች ዛሬም ቀጥለዋል።

ሰልፎቹ በዛሬው ዕለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል ሮቤ እና ሞጆ ከተሞች ተካሄደዋል።

ነዋሪዎቹም ለውጡን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚደግፉ መፈክሮች አሰምተዋል።

በአሶሳ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ፥ በዶክተር ዐቢይ አሕመድ መሪነት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስክ የተመዘገቡ ጅምር ስኬቶች የዓለምንና የሀገሪቱን አካባቢዎች ትኩረት የሳቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሠልፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ ሀገር የምትገነባው በተናጠል ሳይሆን በጋራ በመሆኑ በመደመር የሀገርን ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል ማለታቸውን ከሁለቱ ክልሎች የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version