አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የዓድዋ ድል በዓል ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ “በሚኒሊክ አደባባይ አይከበርም” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ተናግረዋል፡፡
በዓሉ ከዚህ ቀደም አባት አርበኞች በሚኒሊክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው እንደሚያከብሩት ሁሉ ዘንድሮም በዚያው መንገድ ይካሄዳል ነው ያሉት፡፡
የዓድዋን ክብር ወደኋላ የሚመልስ ነገር እንደማይደረግም አረጋግጠዋል፡፡
ህዝቡም ይህን አውቆ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ሊረዳ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የ126ኛው የአድዋ ድል በዓል በነገው እለት ተከብሮ ይውላል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!