ቴክ

ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን የማያነሳው ዘመናዊ ስልክ

By Tibebu Kebede

February 24, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን ለማንሳት የማይፈቅደው ዘመናዊ ስልክ ይፋ ተደርጓል።

“ቶን ኢ 20” የተሰኘው ይህ ዘመናዊ ስልክ ቶን ሞባይል በተባለ የጃፓን ኩባንያ የተመረተ መሆኑ ተገልጿል።

ስልኩ ደንበኞች በማንኛውም መስፈርት ተገቢ ያልሆኑ እና ተቀባይነት የሌላቸው ምስሎችን እንዲወስዱ ፈቃድ አይሰጥም ነው የተባለው።

በዚህ መሰረት ማንኛውም የስልኩ ተጠቃሚ የራሱንም ሆነ የሌላን ሰው ራቁት ምስል እና መሰል ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን ማንሳት አይችልም።

ይህም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን ለመውሰድ ፈቃድ የማይሰጠው የመጀመሪያው ዘመናዊ ስልክ አድርጎታል።

ከዚህ ባለፈም ስልኩ ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም ከጎግል እና መሰል ገጾች ለማውረድ የማይፈቅድ መሆኑ ነው የተነገረው።

ስልኩን ከሌሎች መሳሪያዎች ጋር በማገናኘትም ተገቢ ያልሆኑ ምስሎች በስልኩ ለማንሳት እና ለማውረድ መሞከራቸውን የሚያሳይ መልዕክት የሚያደርስ መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision