የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በህክምና ላይ የሚገኙትን ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

February 28, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በህክምና ላይ የሚገኙትን ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዛሬ ጠዋት በሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች “አቡነ መርቆሬዎስን ፈጣሪ በምህረቱና በቸርነቱ ይፈውሳቸው ዘንድ ከልብ እመኛለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በዙሪያቸው ክብካቤ እያደረጉላቸው ያሉትን የህክምና ባለሙያዎችና አባቶች አመስግነዋል ከንቲባዋ፡፡