Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

9ኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 9ኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የወረዳዎች የስፖርት ውድድር ተጠናቋል፡፡
በስፖርት ውድድሩ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ቡን ዊው እንዳሉት÷ ስፖርት ለጤንነትና ለአካል ብቃት ካለው ጠቀሜታ በተጨማሪ የወንድማማችነትና የአንድነት እሴቶችን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና ይጫወታል፡፡
በክልሉ የተለያዩ የስፖርት ውድድር መርሃ ግብሮችን በመንደፍ፣ ወጣቱ እንዲሳተፍ በማድረግና ውጤታማ የሆኑትን በመለየት በቀጣይ ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ ውድድሮች ማዘጋጀት የውድድሩ አላማ መሆኑንም ነው ገለጹት፡፡
የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ታይዶር ቻንባንግ÷ ክልሉን የሚወክሉ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኅብረተሰቡን የስፖርታዊ እንቅስቃሴ በጥራትና በብቃት በማሳደግ በሀገር አቀፍ መድረኮች የክልሉን ስም ማስጠራት የሚችሉ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ይሰራል ማለታቸውን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዕለቱ በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አዘጋጁ ጋምቤላ ወረዳን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version