አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ ንብረቶችን በማስወገድ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ።
የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ዳአፋል ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ገቢው ባለፉት ስድስት ወራት ከ30 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከተወገዱ ያገለገሉ ንብረቶች የተገኘ ነው።
በዚህም ከ24 መስሪያ ቤቶች 65 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ በማስወገድ 28 ሚሊየን 600 ሺህ ብር ገቢ ተደርጓል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም ከስድስት መስሪያ ቤቶች 580 ያገለገሉ ንብረቶችን እና ከሁለት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን በጨረታ ማስወገድ ተችሏልም ነው ያሉት።
ከኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ፍቼ ቅርንጫፍ ለዝርያ ተገዝተው የነበሩ 14 ኮርማ በሬዎችን በመሸጥ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉንም ተናግረዋል።
በታሪክ አዱኛ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision