Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር ኃይል በሕግ ማስከበርና በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዛሬ እውቅና ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕግ ማስከበር እና በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እውቅና የመስጠት እንዲሁም ለከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ የማልበስ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት እንደሚካሄድ የአየር ኃይል ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል ተሾመ በዳዳ ገለጹ፡፡
በተጨማሪም የቴክኒሻን እና የኤር ፖሊስ ስልጠና ያጠናቀቁ አባላትም በዛሬው ዕለት እንደሚመረቁ ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአየርና ህዋ ህክምና ማእከል፣ የበራሪዎች እና የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ፕሮጀክቶችም ዛሬ የሚመረቁ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version