አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በእንጦጦ እየተሰራ ያለውን የማስዋብ ስራ እና የቱሪዝም መስህብ ግንባታ በዛሬው ዕለት ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅትም በጉለሌ እጽዋት ማእከል፣ በአካባቢው ውስጥ የሚገኘው አረንጓዴ ስፍራ እና እንጦጦ የሚገኘውን አረንጓዴ ስፍራ በአንድ ላይ የሚያስተዳድር ተቋም እንዲመሰረት መወሰኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ ቦታዎቹ ለነዋሪዎች ማረፊያና ለቱሪዝም አገልግሎት እንዲውሉና ስፍራዎቹን በተቀናጀ መልኩ ለመምራ እንዲያስችል ነው የሚመሰረተው።
በተጨማሪም ከሽሮ ሜዳ – ቁስቋም እየተገነባ ያለውን 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ጎብኝተዋል።
የመንገዱ ግንባታ በመጓተቱ ምክንያት ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።
ኢንጀነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው መንገዱ በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
መንገዱን ተከትለውያሉ የባህል ልብስ መሸጫ ሼዶችም በዘመናዊ መልኩ በአዲስ መልክ ተገንብተው ለነባር ባለቤቶቻቸው እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።