Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በግዳጅ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት የምስጋናና የዕውቅና ዝግጅት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ የመረጃ ዋና መምሪያ በግዳጅ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት የምስጋናና የዕውቅና ዝግጅት ተካሄደ፡፡

በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የመረጃ ዋና መምሪያ ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ብርሀኑ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት የሜዳይና የማዕረግ ዕድገት እንደሚሰጥ ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version