የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

By Alemayehu Geremew

February 23, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ በጀመረው ስብሰባው በወሳኝ አገራዊ አጀንዳዎችና የፓርቲውሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።