አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በፖላንድ በተደረገ ቱራን የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር በሁለቱም ጾታዎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በወንዶች 3000 ሜትር አትሌት ለሜቻ ግርማ 7:31.09 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር ሰለሞን ባረጋ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ÷ አትሌት ጌትነት ዋለ አራተኛ፣ አድሃነ ካሳይ ሰባተኛ፣ ሀፍቱ ተክሉ ዘጠነኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች 1500 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ 3:54.77 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆናለች፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር አትሌት ለምለም ኃይሉ ሁለተኛ እንዲሁም ፍሬወይኒ ኃይሉ ሦስተኛ፣ አትሌት ሀብታም አለሙ አራተኛ፣ ሂሩት መሸሻ አምስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች 800 ሜትር ደግሞ ትዕግስት ግርማ ሦስተኛ እንዲሁም ወርቅነሽ መሰለ አምስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!