የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በሠላምና ፀጥታ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

February 22, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ሞሀመድ አህመድ አል ቦዋርዲ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በምስራቅ አፍሪካና በባህረ-ሰላጤው ስላለው የሠላምና ፀጥታ ሁኔታ መምከራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ሁለቱ ሀገራት በሠላምና ፀጥታ ዘርፍ በጋራ በሚሰሩበት እና ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።