አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት በተካሄደው የራስ አል ካምሃ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ግርማዊት ገ/እግዚአብሄር አሸንፋለች።
አትሌት ግርማዊት ገ/እግዚአብሄር 1:04:14 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድርን ያሸነፈችው፡፡
በዚሁ ውድድር አትሌት ቦሰና ሙላቴ 1:05.46 በሆነ ሰዓት በመግባት 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች በተካሄደ ውድድር ሰይፋ ቱራ 58:36 በሆነ ሰዓት በመግባት 4ኛ ደረጃን ሲይዝ÷ አምደወርቅ ዋለልኝ 58:40 በሆነ ሰዓት በመግባት 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!