አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ በእስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ተወካይ ከሆኑት አቶ ዳምጠው ደሳለኝ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚህ ወቅት አምባሳደር ረታ ዓለሙ፥ ኢትዮጵያ በድርጅቱ ተቋማት ያላትን ንቁ ተሳትፎ በመጥቀስ ፣ በተለይ ከተመድ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የሚደረገው ትብብር ትልቅ ሚና እንደምትጫወት ገልጸዋል።
በውይይቱ አቶ ዳምጠው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ በርካታ ስደተኞች የምታስተናግድ በመሆኑ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ያላት ተሳትፎ ከፍ ያለ ግምት እንደሚሰጠው በማንሳት ከኤምባሲው ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
በቀጣይም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየትና ትብብር ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share