Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ የባንክ ስርዓት በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራን ነው – አቤ ሳኖ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ የባንክ ስርዓት በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ አቤ ሳኖ፥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻሻያዎችን በማድረግ የተሻለ የባንኪንግ ሲስተም ተግባራዊ በማድረግ በሀገር ውስጥ ቀዳሚ ባንከ መሆን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የባንኩ ሪፎርም አንድ አካል የሆነው የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ መመረቁን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፥ በአዲስ አበባ እና በክልል የቅርንጫፍ ህንፃዎችን ለመግንባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተመረቀው የዋና መስሪያ ቤት ዘመናዊ ህንፃም ሁሉንም የባንክ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲሰጡ በማድረግ ለደንበኞች፣ ለባንኩ ሠራተኞች እና አመራሮች ለሚያከናውኑት ስራ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎችን ክትትል ለማድረግ አስቸጋሪ እንደነበር ገልፀው፥ በተመረቀው ዋና መስሪያ ቤት ችግሩ እንደሚቀረፍ ተናግረዋል፡፡
ከብድር አሰጣጥ እና አመላለስ ጋር ተግዳሮቶች እንደነበሩ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፥ የወጣቶችን የፈጠራ ሀሳብ ለመደግፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ነው ያሳወቁት፡፡
እስካሁን ዜጎች ብድር ለማግኘት ንብረት ማስያዝ ይጠበቅባቸዉ እንደነበር አስታውሰው፥ ዜጎች የሚያሲይዙት ንብረት ታይቶ ሳይሆን ያላቸውን የፈጠራ ሀሳብ ለመድገፍ ብድር እንደሚመቻች ይደረጋል ብለዋል የባንኩ ፕሬዚዳንት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version