አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልላዊ መንግሥት ክልሉ የገጠመው የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ የፀጥታ መዋቅር ላይ ያሉ ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን አስመልክቶ በዝርዝር ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቷል።
በመሆኑም ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን አሚኮ ዘግቧል።
በዚህም መሰረት፦
1- የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፥ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የፀጥታ አማካሪ
2- የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ሆነው
መሾማቸው ተገልጿል።