የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

February 17, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ለኦሮሚያ ክልል በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ማስረከባቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡