የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 16, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ዩታ ኧርፒላይነን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከኮሚሽነር ዩታ ኧርፒላይነን ጋር ተገናኝተው ኢትዮጵያ ለዕድገቷ የምታደርጋቸውን ጥረቶች በተመለከተ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፥ የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽን እና ኢትዮጵያ አጋርነታቸውን ለማጠናከር በሚያስችሉ አካሄዶች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!