አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በኤፍ ኤስ አር የጭነት መኪና ተጭኖ ሊገባ የነበረ 2 ሺህ 500 የክላሽ ጥይት በጉለሌ ክፍለ ከተማ የፍተሻ ኬላ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፥ በፍተሻው ወቅት በጥይት አዘዋዋሪነት የተጠረጠረው ግለሰብና አሽከርካሪው ለጊዜው ቢሰወሩም ፖሊስ ክትትሉን ቀጥሏል ብለዋል።
ተሽከርካሪው እና ጥይቶቹ በቁጥጥር ሥር ውለው በኤግዚቢትነት የተያዙ ሲሆን፥ የፖሊስ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!