Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ቱርክ በ13 የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመተባበር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣የካቲት 9፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ቱርክ በ13 የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ለመስራት መስማማታ ቸዉን አስታወቁ፡፡

የቱርኩ ፕሬዚደንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻን ከአስር አመታት በኋላ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ ከአቡዲያቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዚያድ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡

ወይይታቸውን አስመልከተው ሼክ ሞሀመድ ቢን ዚያድ እንደተናገሩት፥ በተደረገው ውይይት የሀገራቱን የንግድ ልውውጥ በእጥፍ ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት የፀጥታ እና ወታደራዊ አቅማቸዉን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት መስማማታቸዉ ተገልጿል፡፡

ቱርክ ልዑካን ቡድን አበላት ሆነው በኤምሬትስ የተገኙ የመንግስት ተወካዮች ከአቻዎቻቸው ጋር በጤና እና በሕክምና ሳይንስ፣በባሕር ሀይል ፣በኢንዱስትሪ ቴክኖሎጅ፣ በአየር ንብረት ለዉጥ ፣በንግድ እና ኢኮኖሚ በአጠቃላይ በ13 የኢኮኖሚ ዘርፎችና በኢንዱስትሪ በጋራ ለመስራት መስማማታቸዉን የኤምሬትሱ ዘናሽናል የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version