Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ካለፉት ሣምንታት ጀምሮ ሸገር ዳቦ ምርት ማቅረብ አልቻለም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድ ወር ከ15 ቀን በላይ የዳቦ አቅርቦት መቋረጡን የሸገር ዳቦ መሸጫ ሱቆች ሠራተኞች እና ተጠቃሚዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናገሩ፡፡

በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የዳቦ አቅርቦቱ መቋረጥ ለችግር እንደዳረጋቸው እና ሠራተኞችም ሥራ በማቆማቸው መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑር በበኩላቸው፥ ከሰሞኑ ዳቦ ማቅረብ ያልተቻለው ከግብዓት ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እስከሚሰጥ በመጠበቃቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በፍጥነት ቀርፎ ፋብሪካው ወደ ሥራ እንዲመለስ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በዓመት 309 ሚሊየን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጸው÷ 50 በመቶ ደግሞ በፋብሪካው ተሸፍኖ ለከተማዋ ነዋሪዎች ዳቦ ይቀርብ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኮሙኒኬሽን እና የማስታወቂያ ኃላፊ አቶ መኮንን ተሾመ በግብዓት እጥረት የዳቦ ምርት ማቅረብ እንዳልተቻለ ገልጸው፥ በቅርቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩ እንደሚፈታ እና ወደ ስራ እንደሚገቡ አረጋግጠዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version