አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ ከየመን የተወነጨፉ በርካታ ሚሳኤሎች ማክሸፏን አስታወቀች።
ሳዑዲ መራሹ ጥምር ጦር እንዳስታወቀው፥ ሚሳኤሎቹ ከየመን ሃውቲ አማጽያን የተወነጨፉ ናቸው።
ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው የተባሉት ሚሳኤሎች ከመዲናዋ ሰንዓ መወንጨፋቸውን የሳዑዲ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለስልጣናቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የጥምር ጦሩ ቃል አቀባይ ተርኪ አል ማሊኪ በበኩላቸው ሊፈጸም የታሰበው ጥቃት ዓለም አቀፍ ህጎችን የጣሰና ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ እንደነበር ተናግረዋል።
የሃውቲ አማጽያን እስካሁን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ያሉት ነገር የለም።
ሳዑዲ ቴህራን የሃውቲ አማጽያንን በመደገፍ ለሚሰነዘርባት ጥቃት ዋነኛ ተዋናይ ናት በሚል ትወነጅላለች።
ቴህራን በበኩሉ ውንጀላውን በተደጋጋሚ ታስተባብላለች።
ምንጭ፦ አልጀዚራ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision