አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የዓለም ጤና ድርጅት አጠቃላይ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ባውሬማ ሃማ ሳምቦ ተፈራርመውታል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን ተደራሽነት፣ በድንገተኛ ህክምና አገልግሎት እና በጤና ማበልጸግና አጠቃላይ የጤና ስርዓቱን ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ተገልጿል።
በተያያዘም የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ስራዎችን የሚያግዙ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
የህክምና ግብዓቶቹ 43 ሺህ ዶላር ግምታዊ ዋጋ አላቸው።
ግብዓቶቹ ለጤና ባለሙያዎች የስራ ላይ የደህንነት መጠበቂያ እንደሚያገለግሉም ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision