የሀገር ውስጥ ዜና

የሳይበር ደኅንነትን ለማስጠበቅ አስቻይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

By Meseret Awoke

February 15, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ የኤጀንሲውን የሳይበር ተሰጥዎ ልማት ማዕከል፣ በኤጀንሲው ለምተው በዲጂታል ኤግዚቪሽን ማዕከል የቀረቡ ምርት እና አገልግሎት እንዲሁም የኤጀንሲውን ሠራተኞችና ኃላፊዎችን ቢሮ መጎብኘታቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሚኒስትሩ ከኤጀንሲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ የሳይበር ደኅንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የምርምር፣ ልማት እና ስልጠናዎች ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳይ ትኩረት አድረገው መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!