Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስ የሶማሌ ክልል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታውቋል፡፡

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑንም የክልሉ መንግስት አመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ በሰላም እና መረጋጋት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት ጋር በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ ጋር በመተባበር መክሸፉን አስታውቋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version