Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሶማሌ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ለዘላቂ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ከክልሉ ጋር በቅንጅት ይሰራል-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ለዘላቂ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ከክልሉ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንቷ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ ለተፈቀሉ በርካታ ዜጎች የውሃ አቅርቦት መሰራጨት እንዳለበት አንስተዋል፡፡
 
በቅርቡ በአካባቢው ባደረጉት ጉብኝትም በቀብሪ በያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በተለይም ሴቶች የውሃ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን እንደገለጹላቸው አስታውሰዋል፡፡
 
ለዚህ ጥያቄያቸው ምላሽም ጽህፈት ቤታቸው በአካባቢው በድርቅ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች ለአንድ ወር በቀን አምስት ቦቴ ውሃ ድጋፍ ማሰራጨት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
 
ችግሩን በፍጥነት ለመቆጣጠርም ለዘላቂ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ነው ፕሬዚዳንቷ የገለጹት፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
Exit mobile version