Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን የመከላከል አቅም ከ96 ከመቶ በላይ ደርሷል -ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን የመከላከል አቅሙ ከ96 ከመቶ በላይ መድረሱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሩ የኤጀንሲውን የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም፥ የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ስራ የመመለስ አቅሙ ማደጉን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን ጠቁመው፥ እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች ቢደርሱ እንደሃገር ከፍተኛ ጉዳት ይደርስ ነበር ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን የመከላከል እና ምላሽ የመስጠት አቅሙ 96 በመቶ መድረሱን ነው ያሳወቁት።
በዋናነት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ሚዲያዎች ለሳይበር ጥቃት ኢላማ የተደረጉ ተቋማት መሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል ።
በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከገፁ አደሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን ገልፀዋል።
የሚዲያ ተቋሙ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን ሃገር ውስጥ አለመሆኑን ዶክተር ሹመቴ በጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ጠቁመው፥ የፌስቡክ አካውንቱን አክሰስ እንዲያደርጉ ሃላፊነት የወሰዱ አካላትም ለጥቃቱ መከሰት ሚና ነበራቸዉ ብለዋል።
በተለይም አንዱ የፌስቡክ አድሚን የተላከለትን አጥፊ ተልእኮ ያለውን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version