አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠ/ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩጋንዳ በተከበረው 41ኛው የሰራዊት ቀን ላይ ተገኙ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሬ ሙሴቪኒ ባደረጉላቸው የክብር ግብዣ ነው።
በወቅቱ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘታችሁ አመሠግናለሁ ብለዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላንም እንኳን ደስ አለዎ ብለዋቸዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሀኑም÷ ለተደረገላቸው የክብር ግብዣ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ በዝግጅቱ ላይ ከተገኙ ከዩጋንዳ፣ ከብሩንዲ፣ ከሞዛምቢክ፣ ከደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች እንዲሁም ከሩዋንዳ፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከኬንያ ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች ጋር በተናጠል ተገናኝተው መክረዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በውይይታቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስረድተው÷ በቀጣይም በሁለትዮሽ ግንኙነት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!