Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሽብር ቡድኑ ህወሃት የተሰጠውን የሰላም እድል ካልተጠቀመ ሰራዊቱ በማንኛውም ጊዜ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው – ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የሰጠውን የሰላም ጥሪ እየጣሰ የሚገኘው ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ ተቆጥቦ ወደ ሰላማዊ መንገድ ካልመጣ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ወታደሩ ዝግጁ መሆኑን የመከላከያ የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ገልጸዋል።

ዛሬ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታቂ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ ተደርጓል።

ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ሀገርና ህዝብን ሲበዘብዝ ቆይቶ በመጨረሻም በህዝብ እምቢተኝነት ከስልጣን መወገዱ በገለጻው ወቅት ተነስቷል።

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮችና የኢጋድ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፥ ሽብርተኛው  ህወሓት እኔ ያልኩት ብቻ  ካልሆነ ሀገር መፍረስ አለበት ብሎ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጅ ከቆየ በኋላ የሰሜን እዝን መውጋቱን  አስታውሰው፥ መንግስት ተገዶ ህግ የማስከበር እርምጃ ውስጥ መግባቱን አብራርተዋል።

ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከጣልቃ ገብነት ነጻ ነው፣ በመግባባትና በመረዳዳት ላይ የተመሰረት ሰላምን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ያላት ኢትዮጵያ የሰላም ሀገር መሆኗን በተለያየ ጊዜ አሳይታለች ብለዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት ለተለያዩ ሀገራት በሰላም ማስከበር  ላይ በመሰማራት ለሰላም ዋጋ ከፍላለች፤ ለሰላም ሁሌም ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

ሽብርተኛው ቡድን የተሰጠውን የሰላም እድል ካልተጠቀመ ግን ሰራዊቱ በማንኛውም ጊዜ በዚህ ቡድን እርምጃ መውሰድ በሚችልበት ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version