አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ የተካሄደውን የአክሰስ ባንክ ሌጎስ ከተማ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ አሸነፉ።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ስራነሽ ዳኜ አንደኛ ስትሆን፥ አትሌት አለምነሽ ሂርፓ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ኬንያዊቷ ናኦሚ ማዮ በውድድሩ ሶስተኛ መሆኗም ተገልጿል።
በወንዶች በተካሄደው የሌጎስ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ዴሬሳ ገለታ ኡልፋታ፣ ኬንያውያኑ ዴቪድ ባርማሲ እና ኢማኑኤል ናቤን በማስከተል አሸንፏል።
ኬንያዊው አትሌት ዴቪድ ባርማሲ ከሁለት አመት በፊት ባስመዘገበው (2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ23 ሴኮንድ) ጊዜ የሌጎስ ማራቶን የቦታው ክብረወሰን ባለቤት ነው ተብሏል።
የአክሰስ ባንክ ሌጎስ ከተማ ማራቶንን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ሲያሸንፉ በፈረንጆቹ ከ2019 በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
በወቅቱ በወንዶች አትሌት ስንታየሁ ለገሰ እና በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት መሰረት ድንቄ አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል።
የሌጎስ ማራቶን ውድድር በፈረንጆቹ 2016 የተጀመረው ሲሆን÷ በሴቶች ከተካሄዱት ውድድሮች ኢትዮጵያውያኑ 5 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዘዋልም ነው የተባለው።
በተመሳሳይ ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያውያን ማሸነፍ የቻሉት ዘንድሮን ጨምሮ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!