Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ዛሬ መጠናቀቁን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው÷ ሥልጠናው ከፍተኛ አመራሩ የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት መወጣት ይችል ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የሥራ አፈጻጸም፣ የሥነ ምግባርና የአገልጋይነት አቅሙን ለማጎልበት የተዘጋጀ ነው።
ከፍተኛ አመራሮቹ በሥልጠናው ህዝቡ የጣለባቸውን ሀላፊነት በከፍተኛ ትጋትና ቁርጠኝነት እንደሚወጡ ገልጸው÷ በየተቋሞቻቸው የአገልጋይነት አመራርን ተግባራዊ በማድረግና የህዝቡን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመመለስ የዜጎቻችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
ተመሳሳይ የአመራር የአቅም ግንባታ መድረኮች በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ መዋቅሮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ ብሏል ጽ/ቤቱ ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version